የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ ነው – አቶ ፈቃዱ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተከናወነ የሚገኘው የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ገለፁ፡፡
በአቶ ፈቃዱ ተሰማ የተመራ ልዑክ በሰሜን ሸዋ ዞን ቅምቢቲ እና አቢቹኛኣ ወረዳዎች በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል፡፡
በዚህ ወቅትም አቶ ፈቃዱ እየተከናወነ የሚገኘው የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ በስንዴ ልማት ላይ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡