ስፓርት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ አሸነፈ

By Tamrat Bishaw

April 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ ሀምበሪቾን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

ቀን 10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማን ለድል ያበቃውን ጎል የሀምበሪቾው ዲንክ ኪያር በራሱ ላይ አስቆጥሯል።

በተመሳሳይ ቀን 1:00 ላይ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።