ስፓርት

ኬንያ በተካሄደ የ5 ሺህ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

By Melaku Gedif

April 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡

ትላንት ማምሻውን በኬንያ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር ጎልድ ውድድር በ5 ሺህ ሜትር አትሌት ማርታ አለማየው አሸንፋለች፡፡

አትሌት ማርታ ርቀቱን 15 ደቂቃ 14 ሰከንድ ከ54 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡

በዚሁ ርቀት አትሌት ለምለም ንብረት 3ኛ ደረጃን ስትይዝ ÷ አትሌት ሺቶ ጉሚ ደግሞ አራተኛ ሆና አጠናቅቃለች፡፡

በተመሳሳይ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ ርቀቱን በ13 ደቂቃ 34 ሰከንድ ከ77 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ አሸንፏል፡፡