የሀገር ውስጥ ዜና

ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ

By Tamrat Bishaw

April 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን እንደማይፈታ የገለጹት የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ÷ ታሪካዊ አጋጣሚ በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በዚህም ትጥቅ አንግበው እየታገሉ ያሉ አካላት ወደ ምክክሩ እንዲመጡ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው÷ አሁንም ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በመጠየቅ ሲመጡም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሚያመቻቻቸው መድረኮችም ማንኛውም ሰው በነጻነት የሚሳተፍባቸው መሆናቸውን አስረድተው÷ ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡