Fana: At a Speed of Life!

የታክስ አስተዳደር ዲጂታላይዜሽን የታክስ ተግዳሮቶችን መቅረፍ ያስችላል – ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር እና ዓለም ባንክ በጋራ ያዘጋጁት የዲጂታል ታክስ አስተዳደር ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ ናይጄሪያ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባቡዌ፣ ኡጋንዳ፣ ማላዊ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሩዋንዳ ተሳትፈዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ÷ ሀገራት በታክስ አስተዳደር ዲጂታላይዜሽን ላይ መነጋገር፣ መፈተሽ እና ምርጥ ተሞክሮን መለዋወጥ እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡

የታክስ አስተዳደር ዲጂታላይዜሽን የታክስ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና የወረቀት አሰራሮችን ለመቀየር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው÷መረጃዎችን የመለዋወጥ መንገድን እንደሚያሳልጠም ተናግረዋል፡፡

ይህ የሚሆነው ዲጂታላይዜሽን ላይ መስራት ሲቻል መሆኑን ገልጸው÷ ሚኒስቴሩ ኤሌክትሮኒክስ ኢንቮይስን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ወደ ስራ ሲገባም የተሻለ ገቢ መሰብሰብ እንደሚቻል ማስገንዘባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡፡

የናይጀሪያ፣ ማላዊ፣ የኡጋንዳ፣ ዛምቢያ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉሙሩክ የሥራ ሃላፊዎች የየሀገራቸውን የዲጂታል የታክስ አስተዳደር እና ሌሎች የአሰራር ተሞክሮዎችን አቅርበዋል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.