የሀገር ውስጥ ዜና

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

April 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮችን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አድርገዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ከሌሎች ኮሚሽነሮች ጋር በመሆን ነው ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እና ሌሎች የኮሚሽኑን ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎች ጋር የመከሩት፡፡

ውይይቱ ሁለቱ ኮሚሽኖች በሚያከናውኗቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሃሳብ ልውውጥ እንደተደረገበት ከምክክር ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡