ስፓርት

 በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸነፈ

By Mikias Ayele

April 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ ሁለቱንም የባህርዳር ከተማ ግቦች በፍጹም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር÷ የወልቂጤን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፉዓድ አብደላ አስቆጥሯል፡፡

በውጤቱ መሰረትም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን 37 በማድረስ  ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ያሉ ሲሆን ÷ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥቦች ወራጅ ቀጠና ላይ ይገኛል፡፡

የክለቦቹ 19ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ የባህርዳር ከተማው የመሃል ክፍል ተጫዋች አለልኝ አዘነን ድንገተኛ ሕልፈት ተከትሎ መራዘሙ የሚታወስ ነው፡፡