Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 4፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር  2ሚሊየን 464 ሺህ  መድረሱን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።

ይህም ሀገሪቷን በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር  ቀዳሚ ሲያደርጋት ብራዚልና ሩስያ ይከተሏታልም ተብሏል።

ከዚያም ባለፈ ሀገሪቱ በወረርሽኙ ምክንያት  112 ሺህ 924 ሞት  ያስመዘገበች ሲሆን ÷በ41 ሺህ 213 ሞት ናይትድ ኪንግደም በሁለተኝነት  በ39 ሺህ 680 ሞት ብራዚል በሶስተኝነት ተቀምጣለች።

ሀገሪቱ የእንቅስቃሴ ማዕቀብ በማላላት ላይ ብትሆንም አሁንም በ21 የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ  የቫይረሱ ስርጭት  እየጨመረ መሆኑን ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ   ጠቁሟል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7 ሚሊየን  ያለፈ ሲሆን ÷በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ   ሰዎች ቁጥር ደግሞ 416 ሺህ መዝለሉን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.