የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በግንባታ ላይ ያለ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Melaku Gedif

April 24, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጊድ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግንባታ ላይ ያለ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አይዳ አወል እንዳሉት÷ በግንባታ ላይ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ ነው አደጋው የተከሰተው፡፡

ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በደረሰው አደጋም የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ሥራ አስፈጻሚዋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

በመላኩ ገድፍ