የሀገር ውስጥ ዜና

በበጋ መስኖ ስንዴ ከ2 ሚሊየን ሔክታር በላይ ሰብል ተሰበሰበ

By Feven Bishaw

April 24, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጋ መስኖ ስንዴ በዘር ከተሸፈነው 3 ሚሊየን ሔክታር ውስጥ 2 ነጥብ 1 ሚሊየኑ መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እስካሁን ከተሰበሰበውም 73 ነጥብ 9 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ከበደ ላቀው ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 120 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመላክተዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን