ሚኒስቴሩ በግንቦት ወር 18 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በግንቦት ወር 18 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል።
ሚኒስቴሩ በግንቦት ወር 23 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 18 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 77 ነጥብ 8 በመቶ ማሳካቱ ተገልጿል።
ይህም የእቅድ አፈፃፀም ከሀገር ውስጥ ታክስ 10 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከውጪ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 7 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል።
አፈፃፀሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ3 ነጥብ 08 ቢሊየን ብር ወይም የ20 ነጥብ 15 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተመላክቷል።
ሚኒስቴሩ የ2012 በጀት ዓመት ያለፉት 11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሲታይ በ11 ወራት ውስጥ 242 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 217 ነጥብ 24 ቢሊየን በመሰብሰብ የዕቅዱን 89 ነጥብ 42 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡
አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 38 ነጥብ 79 ቢሊየን ወይም 21 ነጥብ 74 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።