Fana: At a Speed of Life!

”ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል የሩጫ ውድድር ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ”ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የሩጫ ውድድር ሊካሄድ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ውድድሩን የሰላም ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመቀናጀት ነው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚካሂዱት፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)÷ ከታላቁ ሩጫ አዘጋጆችና ከሰላም ሚኒስቴር ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው በወቅቱ እንዳሉት÷ የሩጫው ዓላማ በሀገሪቱ እየተገኘ ያለውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማሸጋገር ዜጎች በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው፡፡

ውድድሩ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሰላም ጉዳይ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ ለማስተላለፍ ያለመ ነው ብለዋል።

በሰኔ ወር የሚካሄደው የሩጫ ውድድሩ 5 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲስ አበባ ብቻ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን÷ በውድድሩ ለሚያሸንፉ የገንዘብ እና የሜዳልያ ሽልማት እንደሚበረከት ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.