የሀገር ውስጥ ዜና

የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

By Amare Asrat

April 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አል-ዳባይባ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ምሽቱን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡