የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኦርዲን በምስራቅ እዝ በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

By Melaku Gedif

April 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪና ካቢኔያቸው በምስራቅ ዕዝ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት÷ የምስራቅ እዝ በስሩ የሚገኙ ባዶ ባታዎችን በማልማት ረገድ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ሰራዊቱ የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ጎን ለጎን የሚያከናውነው የልማት ሥራ በተሞክሮነት የሚወሰድና በእዙና ክልሉ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑም የክልሉ መንግስት ድጋፉን ያጠናክራል ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄ መሃመድ ተሰማ በበኩላቸው÷ እዙ በከተማው በሚገኙ ሁለት ስፍራዎች ላይ የግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሚከናወኑ ስራዎችም የክልሉ መንግስት እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።