የሀገር ውስጥ ዜና

የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ

By Melaku Gedif

April 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዳባቢያ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካዊያን ሁሉ ኩራት የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዚህ መልክ በመገንባቱ እንደተደሰቱ መናገራቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡