የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ በርኦ ሐሰን ከሊቢያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

April 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ከሊቢያ ትራንስፖርት ሚኒስቴርና ልዑካን ቡድን ጋር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍን በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ከሊቢያ ትራንስፖርት ሚኒስትር መሃመድ ሰላም አልሻቢ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክሰ ዘርፍ ጋር በተያያዘ በጋራ ለመስራት መክረዋል፡፡

አቶ በርኦ ሀሰን ኢትዮጵያ እና ሊቢያ የቆየ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳለቸው ገልፀው ፥ ኢትዮጵያ ከሊቢያ ጋር በባቡር ትራንስፖርት፣ በአቪዬሽን እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።

የሊቢያ ትራንስፖርት ሚኒስትር መሃመድ ሰላም አልሻቢ በበኩላቸው ፥ ሊቢያ በትራንስፖርት መሰረተ ልማት እየሰራችው ያለውን ስራ ለሚኒስትር ደኤታው ማብራራታቸውም ነው የተነገረው፡፡

ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር በአቪዬሽን አካዳሚ ስልጠና እንዲሁም ከአውሮፕላን ጥገና ጋር ተያይዞ አብሮ የመሰራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል::