የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ ለኢትዮጵያ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ገለጹ

By ዮሐንስ ደርበው

April 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የሚሰጠው ድጋፍ ለኢትዮጵያ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከሆኑት ማርክ ሱዝማን እና ቡድናቸው ጋር መወያታቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም ደስታ እንደተሰማቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፣ ጤና፣ በሥርዓተ-ምግብ፣ በአካታች የፋይናንስ ሥርዓት እና በሌሎች ዘርፎች የሚሰጠው ጠቃሚ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ዕድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡

ይህን ትብብር በማላቅ እና በአዳዲስ ዘርፎች በመተባበር እንሰራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።