ስፓርት

በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 4 በመሆን አሸነፉ

By Mikias Ayele

April 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል፡፡

በውድድሩ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር መቅደስ ዓለምሸት 14 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡

አያል ዳኛቸው ከባድ ፉክክር አድርጋ በ16 ማይክሮ ሰከንድ ተቀድማ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ፥ ለተሰንበት ግደይ ሦሰተኛ ደረጃ እንዲሁም ውብርስት አስቻለ አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

በተጨማሪም በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር ሰለሞን ባረጋ 12 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በመግባት ሲያሸነፍ ቢኒያም መሃሪ በአንድ ሴኮንድ ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ በመሆን አጠናቅቋል፡፡