ኮሮናቫይረስ

በ24 ሰዓታት ውስጥ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Tibebu Kebede

June 11, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 670 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።