የሀገር ውስጥ ዜና

ለአርብቶ አደሩ የጤና ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

By Tamrat Bishaw

May 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ35 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚተገበርና ለአርብቶ አደሩ የጤና ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

ፕሮጀክቱ በ4 ክልሎች ውስጥ የሚገኙ 35 የአርብቶ አደር ወረዳዎችን ያቀፈ መሆኑ ተገልጿል።

በስነ ተዋልዶ ጤና፣ በስርዓተ ምግብ፣ የእናቶች እና የህፃናት፣ የአፍላ ወጣቶች ጤና፣ የጨቅላ ህፃናት ጤና እንዲሁም የቤተሰብ ዕቅድን ማዕከል ያደረገው የዚህ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር መካሄዱን የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበው፤ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ጤናው ተጠበቆ እንዲኖር የሚመለከታቸው አካላት ከሚኒስቴሩ ጎን ጥሪ አቅርበዋል።