1 ሺህ 180 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 180 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመላሾች ውስጥ 1 ሺህ 98 ወንዶች፣ 79 ሴቶች፣ 3 ጨቅላ ህፃናት እንዲሁም 228 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተጠቅሷል።
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡