ከ18 ሺህ ለሚልቁ የባሕር ዳር ነዋሪዎች የበዓል ስጦታ ተበረከተ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ18 ሺህ ለሚልቁ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለበዓል መዋያ የሚሆን 9 ሚሊየን 833 ሺህ ብር የዓይነትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ተደረገ፡፡
ድጋፉ ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ፣ ዱቄት፣ ዘይት፣ዶሮ፣ አልባሳት፣ የንፅህና መጠበቂያና ሌሎች ለበዓል አስፈላጊ ቁሶችን ማካተቱ ተገልጿል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በድጋፍ ርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ እየተከናወነ ያለው መተሳሰብና መደጋገፍ አንድነት ያጠናክራል ማለታቸውን የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ድጋፉ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ መሆኑም ተመላክቷል፡፡