Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ፈጥኖ ምርት መስጠት የሚችል የሙዝ ተክል እየለማ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ ፈጥኖ ምርት መስጠት የሚችል የሙዝ ተክል እየለማ መሆኑ ተገለጸ።

የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ በሦስት ወር በሠርቶ ማሳያ ዕድገቱን እንዲጨርስ ተደርጎ ወደ ማሳ ወጥቶ በዱብቲ ወረዳ የለማውን የሙዝ ተክል ጎብኝተዋል፡፡

የክልሉ እንስሳት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢብራሂም መሐመድ በክልል ደረጃ በተለያዩ ወረዳዎች ሙዝ በስፋት እየለማ መሆኑንጠቅሰው ከእነዚህ መካከልም ዱብቲ፣ ሐንሩካ፣ ዱለሳ እና አዋሽ ፈንታሌን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

ለአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ትኩረት በመሠጠቱ ቀደም ሲል ከሦስት ዓመት በላይ ይፈጅ የነበረው ሙዝ በምርምር ተቋማት በመታገዝ ተሻሸሎ የወጣው ዝርያ በአጭር ጊዜ ለምርት መብቃቱን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይነትም በአይሳኢታና አፋምቦ ወረዳዎች አስፍቶ ለማልማት መታቀዱን ነው የጠቆሙት፡፡

በርዕሰ መሥተዳድሩ የተጎበኘው የሙዝ ተክል በ20 ሔክታር ላይ የለማ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.