አቶ አህመድ ሺዴ በፋይናንስ ዘርፍ ምርጥ መሪ ተብለው ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የዓመቱ የፋይናንስ ዘርፍ ምርጥ መሪ በሚል በአፍሪካን ሊደርሺፕ መጽሔት ተመረጡ።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገትና መረጋጋትን የተገኘው ውጤት ተከትሎ ነው በእንግሊዙ የአፍሪካ ሊደርሺፕ መጽሔት በፈረንጆቹ የ2024 ምርጡ መሪ ለመባል የበቁት።
መጽሔቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ እንዳደረገው አቶ አህመድ ሺዴ በፊስካል አስተዳደር፣ ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጥ ኢንቨስትመንት በመሳብ ረገድ የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል።
ሁሉን አካታች የሆነ እድገትና መሰረተ ልማት እንዲረጋገጥ ትኩረት በማድረግ ኢትዮጵያ ያላትን አቅም እንድትጠቀም ትኩረት አድርገው በመስራት አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሆነም ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ እየተደረገ ያለው ለውጥ እውን ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነትም አድንቋል።