Fana: At a Speed of Life!

የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ።

በዓሉ ልዩ ሥርዓተ ጸሎትና ስግደት በማከናወን ተከብሯል።

የስቅለት በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሲከበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተገኝተዋል።

እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ካህናትና ምዕመናን ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.