የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በጫካ ፕሮጀክት እየሠሩ ላሉ ሠራተኞች የእንኳን አድረሳችሁ መልክት አስተላለፉ

By Shambel Mihret

May 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጫካ ፕሮጀክት ላይ እየሠሩ ላሉ ሠራተኞች የእንኳን አድረሳችሁ መልክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጫካ ፕሮጀክት እየሠሩ ላሉ ሠራተኞች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የምሳ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የእንኳን አድረሳችሁ መልክት እንዳስተላለፉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡