የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማዕድ አጋራ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ባስገነባው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ።
አየር መንገዱ ባከናወነው ማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የአየር መንገዱ አመራር አባላትና ሰራተኞች፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በ2015 ዓ.ም ባስገነባው የምገባ ማዕከል ማዕድ ያጋራው አየር መንገዱ፤ ማሕበራዊ ሀላፊነቱን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን እየተወጣ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ አመልክቷል።