Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማትና የዘርፉ አስፈፃሚዎች የ9 ወር ሥራ አፈፃፀም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት፣ የክልል የዘርፉ አስፈፃሚዎችና ባለድርሻ አካላት ያለፉት ዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ በአዳዲስ ኢንቨስትመንት ማስፋት፣ በኢንዱስትሪ ሽግግር፣ በጥናትና ምርምር ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በመድረኩ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የዘርፉ ሞተር በማድረግ ዘርፉን ለማነቃቃት በታቀደው መሠረት የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም የአምራች ኢንዱስትሪ ዋነኛው ሀገራዊ የርብርብ ማዕከል እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.