Fana: At a Speed of Life!

በዋቻ ከተማ የንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዋቻ ከተማ ከ240 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ።

ፕሮጀክቱን የመረቁት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ናቸው።

በመንግስትና በባስኬት ፈንድ በተገኘ ከ240 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ2014 ዓ.ም የተጀመረው የግንባታ ፕሮጀክቱ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት መብቃቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለቀጣዮቹ 50 ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተገነባው የዋቻ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ከ38 ሺህ በላይ የሚሆኑ የዋቻ ከተማ እና የአካባቢውን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.