አቶ አወሉ አብዲ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አወሉ አብዲ ለ #ጽዱኢትዮጵያ 10 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል።
ንቅናቄው ሰዎች ንጽህናውን በጠበቀ ቦታ በመጸዳዳት አካባቢን ንጹህ የማድረግ ባህልን እንዲያሳድጉ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች እንዲሠሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መሆኑ ይታወቃል።
ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ዜጎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የቀጠሉ ሲሆን÷ ከትናንት በስቲያ ብቻ በተካሄደ ዲጂታል ቴሌቶን በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወሳል፡፡