የቻይና ብሔራዊ የቴክስታይልና ጨርቃ ጨርቅ ካውንስል ዘርፉን በተመለከተ በኢትዮጵያ ቅኝት ማድረግ እፈልጋለሁ አለ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ብሔራዊ የቴክስታይል እና ጨርቃ ጨርቅ ካውንስል በኢትዮጵያ የቴክስታይል እና ጨርቃ ጨርቅ ዘርፉን በጥልቀት ለመቃኘት እና ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡
በካውንስሉ ዋና ጸሐፊ ዚያ ሊንግ ሚን የተመራ ልዑክ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀና አርአያስላሴ እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይታቸውም ካውንስሉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ የጨርቃ ጨርቅ ልማቶች እና ያሉበትን ደረጃ የሚያጠና ተቋም መሆኑ መገለጹን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያም በቴክስታይል እና ጨርቃ ጨርቅ ዘርፉን በጥልቀት ለመቃኘት እና ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ካውንስሉ አስታውቋል፡፡
በዘርፉ ያሉ ዕድል እና አማራጮች፣ ማበረታቻዎች እንዲሁም የፖሊሲ ማሻሻያዎች ላይም ለልዑኩ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡