Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ የሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን እየሰራሁ ነው አለ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈን እየሰራሁ ነው ሲል ገልጿል፡፡

በጎርጎራ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት የ9 ወር ስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አጽዕኖት ከሰጡባቸው ጉዳዮች አንዱ ይህ ነው፡፡

የኢፌዲሪ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንም እንደ መንግስት የተያዘው ሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም መሆን አለበት የሚለው አቅጣጫ ተግባራዊ እንዲሆን ስራዎችን መስራት ጀምሪያለሁ ብሏል፡፡

ለዚህም የአደጋ ስጋት ፕሮፋይል በሚል በ600 ወረዳዎች ላይ የተጋላጭነት ጥናት ተሰርቷል፤ጥናቱ መነሻ የሚያደርገው ተጋላጭነት ላይ ቀድሞ መስራት ከተቻለ የሚወጣው ኢንቨስትመንት ከጉዳት በኋላ ከሚወጣው በብዙ እጥፍ ማዳን ይቻላል በሚል ጭምር ነው፡፡

ስለዚህ “በራስ አቅም ሰብአዊ ድጋፍ” የሚለው አቅጣጫ አንዱ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም(ዶ/ር)፡፡

ለማሳያነት ባለፈው አመት 4 ቢሊየን ለሰብአዊ ድጋፍ አስፈልጎ 33 በመቶ ያህል ነው ከአጋር አካላት የተገኘው ÷ይህም ማለት በራስ አቅም በአብዛኛው የመሸፈን አቅም እየተፈጠረ መጥቷል ነው ያሉት፡፡´

ጠቅላላው ስሌት ሲሰራ ደግሞ ለድጋፍ 20 ሚሊየን ኩንታል ምርት በዓመት ያስፈልጋል፤ይህን ለማምረት የሚያስፈልገው 250 ሺህ ሄክታር መሬት መሆኑ ተለይቷል፡፡

ይህን በየክልሉ በማከፋፈል የማምረት እንቅስቃሴው ሲጀመር ችግሩን 99 በመቶ መቅረፍን ታሳቢ አድርጎ ነው፡፡

በተባለው ደረጃ ምርቱን በማምረት 500 ሺህ ሜትሪክ ቶን መጠባበቂያ እና 1ነጥብ5

ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የዕለት ደራሽ ለማከማቸት ታስቧልም ነው ያሉት።

ለዚህም የተለያዩ አማራጮች ተቀምጠው ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)ም ኢትዮጵያ እራሷ አምርታ መመገብ ትችላለች ሲሉ ለተግባራዊነቱ ስራ አስፈጻሚው እንዲተጋ አሳስበዋል፡፡

በኃይለኢየሱስ ስዩም

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.