Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን በሶማሌ ክልል ለሚገኙ ስደተኞችና ለተቀባይ ማህበረሰቡ የሚሆን የ37 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን በሶማሌ ክልል ለሚገኙ የሌላ ሀገራት ስደተኞችና ለተቀባይ ማህበረሰቡ የሚሆን የ37 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡

በፈረንጆቹ ሕዳር 14 ቀን 2024 በጎ ጎረቤቶች በሚል በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በጃፓን መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገውን “የአው-ባሬ እና የሸደር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን እና አስተናጋጅ ማህበረሰብን የማስተዋወቅ ፕሮጀክት” የመክፈቻ ስነ-ስርዓት መዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡

በክልሉ ፋፋን ዞን የሚገኙ አው-ባሬ እና ሸደር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ከ15 ዓመታት በላይ በርካታ ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ።

አብዛኛዎቹ ስደተኞች ቋሚ ስራ የሌላቸውና በዋነኛነት በውጭ እርዳታ ላይ ጥገኛ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ከዚህ በተጨማሪ በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ረዘም ያለ ጊዜ ቢቆዩም የስደተኞቹ የኑሮ ሁኔታ እንዳልተሻሻለም ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም 88 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች አሁንም በድንገተኛ ጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ እንሚገኙ የጠቀሰው ኤምባሲው ፥ ለጤና እና ሌሎች በርካታ አደጋዎች ተጋላጭ መሆናቸውንም ተጠቅሷል፡፡

በዚህም ምክንያት ነው ጃፓን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለሚገኙ የሌላ ሀገራት ስደተኞችና ለተቀባይ ማህበረሰቡ የሚሆን የ37 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገችው ተብሏል።

ይህ ድጋፍ ለስደተኞቹ እና ለተቀባይ ማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና የአኗኗር ሁኔታቸውን ለመቀየር ፋይዳ እንደሚኖረው መገለጹን በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ የላከው መግለጫ አመልክቷል።

በዚህ መንገድ ፕሮጀክቱ ስደተኞች የመኖሪያ አካባቢያቸውን፣ ኢኮኖሚያዊ እድገታቸውን በማሻሻል ከእርዳታ ጥገኝነት እንዲወጡ እና በራሳቸው የሚተማመኑ እንዲሆኑ እንዲሁም ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.