Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሙያ ማህበራት የጤና ልማት ፖሊሲ ትግበራ ላይ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል – ዶ/ር መቅደስ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሙያ ማህበራት የጤና ልማት ፖሊሲ ትግበራ ላይ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ አስገነዘቡ።

ሚኒስትሯ ከጤና የሙያ ማህበራት ፕሬዚዳንቶች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ጤና ሚኒስቴር የሙያ ማህበራት የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ለማሳደግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

የጤና ሙያ ማህበራቱ የጤና አገልግሎት ጥራትን ማሳደግ፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን ማረጋገጥ እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ አሰጣጥን ለማጠናከር ከሚኒስቴሩ ጋር በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ለጤናው ዘርፍ ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ አፈፃፀም ሚናቸውን መወጣት፣ የታካሚ እና የባለሙያ ደህንነትን ጨምሮ የጤና አገልግሎቶችን ጥራት ማሻሻል እና የስራ እድሎችን መፍጠር ላይ ከሚኒስቴሩ ጋር ያላቸውን ስልታዊ ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሙያ ማህበራት እና አካባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮች ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው በመድረኩ መጠቆማቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.