Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ድጋፏን እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን የአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ኮሚሽነሩ÷ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ተልዕኮውን ለማሳካት የዝግጅት ምእራፍ ስራዎችና የመጀመሪያ ዙር የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም የቅድመ ትግበራ ሥራዎችን ሒደት አብራርተዋል።

በዚህም የሃብት አሰባሰብ፣ አጋርነትና ትብብር ሥራዎች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለልዩ መልዕክተኛው አስረድተዋል፡፡

እስካሁን የአሜሪካ መንግስት እያደረገ ላለው ድጋፍና ትብብር አመስግነው÷ በቀጣይ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር በበኩላቸው÷ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም በኢትዮጵያ መንግስት እየተከናወኑ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቅ እና የትግበራ እንቅስቃሴ በመልካም ሒደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሮግራሙ በዕቅዱ መሰረት እንዲሳካ የአሜሪካ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.