Fana: At a Speed of Life!

ፊል ፎደን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) – የማንቼስተር ሲቲ አማካይ ፊል ፎደን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡

የ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ በውድድር ዓመቱ ለማንቼስተር ሲቲ 17 ጎሎችን ሲያስቆጥር 8 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

በዚህም ወጣቱ አማካይ በውድድር ዓመቱ  ከአርሊንግ ሃላንድ በመቀጠል ለውሃ ሰማያዊዎቹ ብዙ ጎል ያስቆጠረ ተጨዋች መሆን ችሏል፡፡

ከሽልማቱ በኋላ ፎደን በአለም ምርጥ በተባለው የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የዓመቱ  ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን ማሸነፍ ለኔ ትልቅ ስኬት ነው ብሏል፡፡

ያለ ቡድን አጋሮቼ ይህ ስኬት አይታሰብም ያለው ፎደን በማንቼስተር ሲቲ  ስታፍ አባላት፣አሰልጠኞች እና ተጫዋቾች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ቀደም ሲል በተደረጉ ምርጫዎች የአርሰናሉ በረኛ ዴቪድ ራያ የዓመቱ ምርጥ በረኛ ሽልማትን፣የቼልሲው አማክይ ኮል ፓልመር ደግሞ የውድድር ዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.