Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በበልግ ወቅት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ ለምቷል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በበልግ ወቅት ብቻ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ ለምቷል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የግብርና ሽግግር ማረጋገጥ የትኩረት ማዕከል አድርገን ከተነሳን ጊዜ አንስቶ አንፃራዊ ስኬት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በለውጡ ጉዞ ግብርና ላይ በተደረገው ትኩረት በተለያዩ ምርቶች ራስን ከመቻል አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በዚህ ዓመትም በበልግ ወቅት ብቻ ከ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ መልማቱን እና ጥሩ የሚባል ምርትም እየተገኘ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በግብርናው ዘርፍ የተገኘው የእስካሁኑ ስኬቱ አበረታች ቢሆንም ከህዝባችን ቁጥር፣ ፍላጎትና ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሲታይ ገና ከመነሻችን አልራቅንም ሲሉም ተናግረዋል።

በመሆኑም በግብርና ዘርፍ የተጀመረውን ስራ በብዙ እጥፍ ማሳደግ፣ ምርታማነት ላይ በእጅጉ መስራት እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ጋር ጠንካራ ትስስር መፍጠር ላይ መስራት ይገባል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.