Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የትምህርት ፎረም ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በብሪታንያ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፉ የትምህርት ፎረም ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በፎረሙ ላይም በትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልዑክ ፎረሙላይ በሚኖረው ቆይታም ከተለያዩ የትምህርት ልማት አጋር ድርጅቶች ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር እንደሚመክር ይጠበቃል መባሉን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ከዋናው ፎረም በተጨማሪ በሚኖሩ የጎንዮሽ ውይይቶችም የኢትዮጵያን የትምህርት ሪፎርም ሊደግፉ በሚችሉበት ሁኔታዎች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.