Fana: At a Speed of Life!

የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት በአፋር ክልል ይፋ ተደርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ የስንዴ ምርታማነትን ማሳደግ እና አርሶ አደሩ በዘርፉ ያለውን ገቢ በማሳደግ ሕይወቱን እንዲያሻሽል ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በዋናነት በአፋር፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በሚገኙ 76 ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ በበጋ እና በክረምት እንዲሁም በሌሎች ወቅቶች ስንዴን ማምረት የሚያስችል ትልቅ አቅም እንዳላት ተናግረዋል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታትም በስንዴ ልማት ዘርፍ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ነው የተናገሩት፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በበኩላቸው÷ በቤተሰብ እና በሀገር ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት በተደረገው ጥረት ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአፋር ክልል የሚገኙ አርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደሮችን ሕይወት ለማሻሻል ሚናው የጎላ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.