230 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦማን ማቆያ ጣቢያዎች የነበሩ 230 ኢትዮያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከኦማን ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 1 ሺህ 150 ኢትዮጵያውያን መመለሳቸውም ተገልጿል፡፡