ኢትዮጵያ እና አውስትራሊያ በትብብር የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችላቸው ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአውስትራሊያ መንግስት በጋራ በስርዓተ-ፆታ እኩልነት ሴቶችን ማብቃት፣ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እንደገለፁት ፥ የአውስትራሊያ መንግስትና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅነት ያላቸው ሀገሮች እንደሆኑ ገልፀዋል ።
የአውስትራሊያ መንግስት ለሚኒስትር መስሪያቤቱ እያደረገ ላለውን ገንቢ አስተዋጽዖ ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይ በሁሉም ደረጃዎች የሴቶችን አመራር ተሳትፎ ማሳደግ፣ ሴቶች በሰላም ግንባታ ሂደት ማሳተፍ፣ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ፣ የስርዓተ-ፆታ እኩልነትና ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በሚመለከት በጋራ ለመስራት ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ አድሎአዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ የሚሰራ ኮሚቴ (ሲኢዲኤደብሊው) ከፈረንጆች 2025 እስከ 2028 በድጋሚ ለመመረጥ የአውስትራሊያ እጩ ናታሻ ስቶት ዴስፖጃ በበኩላቸው ፥ አውስትራሊያ በጾታ እኩልነትና በሴቶች ማብቃት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሪ ለመሆን እንደምትሰራ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በስርዓት ፆታ እኩልነትና በሽግግር ፍትህ ረገድ ያስመዘገበችው ውጤት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው ፥ በቀጣይም ሚኒስቴሩ ጋር ለመስራት ተስማምተዋል።