Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጣሊያን ወታደራዊ ተቋማትን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው የኢትዮጵያ የመከላከያ ልዑክ በጣሊያን የተለያዩ የወታደራዊ ኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ተቋማትን ጎብኝቷል፡፡

በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው የኢትዮጵያ የመከላከያ ልዑክ በጣሊያን ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

የጣሊያን የምድር ኃይል እና አየር ኃይል ስር በሚገኙ የተለያዩ ወታደራዊ ተቋማትን የጎበኙት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሁለቱ ወገኖች መካከል ባለው የወታደራዊ ትብብሮች መሠረት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የተደረገው ጉብኝት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገው ውይይትም የጣሊያንን የዘርፉ ቴክኖሎጂ ደረጃ ለመረዳት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን ÷በሁለቱ ሀገራት መሰል ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ከመግባባት ላይ መደረሱን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.