Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 268 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)  ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 644 የላብራቶሪ ምርመራ 268 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጡት ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታትም ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በዚህም በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 55 ደርሷል፡፡

እንዲሁም  በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 166 መድረሱ ነው የተነገረው።

ቫይረሱ በምርምራ የተገኘባቸው ሰዎች 177 ወንዶች እና 91 ሴቶች ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 90 መሆኑ ተጠቁሟል።

በዜግነት 267ቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ አንዱ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችም  232 ከአዲስ አበባ ፣ 12 ከኦሮሚያ ክልል፣ 8 ሰዎች ከአማራ ክልል ፣ 6 ሰዎች ከትግራይ ክልል ፣ 5 ሰዎች ከሀረሪ ክልል ፣ 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ፣ 2 ሰዎች ከአፋር ክልል እና 1 ሰው ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መሆናቸውን በጋራ ያወጡት ሪፓርት አመልክቷል።

በሌላ መልኩ በትላንትናው  44 ሰዎች 28 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከአማራ ክልል፣ 4 ከአፋር ክልል፣ 3 ከኦሮሚያ ክልል እና 3 ከሐረሪ ክልል ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 495 ደርሷል።

ከዚህ ባለፈ በሰኔ 4 ቀን ሪፖርት በተደረገው የዕለታዊ መግለጫ ቫይረሱ በምርመራ እንድተገኘባቸው ከተገለፁት ሰዎች መካከል 17 ሰዎች ከዚህ ቀደም ሪፖርት ተደርገው በህክምና ማዕከል ውስጥ ያሉ እና ለክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

ለዚህም ይቅርታ የጠየቁት ተቋማቱ  ሰኔ 4 ዕለት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 147 መሆናቸውን አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.