የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች በ10 እጥፍ መጨመሩ ተገለፀ

By Tibebu Kebede

June 13, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አንድ ወር ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ መጨመሩን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት አስታውቋል።

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ብዛት 250 የነበረ ሲሆን ባለፈው አንድ ወር ብቻ በ10 እጥፍ እንደጨመረ ነው የታወቀው።