Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የስራ ዕድል ለተመቻቸላቸው ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መሰጠቱ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ 10 ወራት የስራ እድል ለተመቻቸላቸው ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መሰጠቱን የክልሉ ስራና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ አወቀ ዘመነ እንደገለጹት÷ በበጀት ዓመቱ 10 ወራት 609 ሺህ 697 ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።

ከተፈጠረው የስራ እድል ውስጥ 418 ሺህ 343 የሚሆነው ቋሚ የስራ ዕድል መሆኑ ወቅታዊ የክልሉን ችግር በመቋቋም የተሰራው ስራ የሚበረታታ እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል።

የስራ እድል የተፈጠረላቸው ዜጎች 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የብድር ገንዘብ እንዲሁም 6 ሺህ 600 ሄክታር መሬት ለማምረቻና ለመሸጫ ቦታ መሰጠቱን አብራርተዋል።

በተመቻቸው የብድር አቅርቦት በ14 ሺህ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ 20 ሺህ አንቀሳቃሾች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን አመልክተው፤ የስራ እድል ፈጠራ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.