በመዲናዋ በሚካሄደው የምክክር ምዕራፍ ለሚሳተፉ አካላት ገለጻ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ በሚካሄደው የምክክር ምዕራፍ ለሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ ገለጻው ከግንቦት 21 እስከ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የምክክር ምዕራፍ÷ ባለድርሻ አካላት ከኮሚሽኑ ጋር ተባብረው የሚሰሩበትን የአሠራር ሥርዓቶች እና የምክክር ሂደቶችን በተመለከተ ግንዛቤን ለማስጨበጥ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡
በገለፃውም ከመንግስት ሠራተኞች፣ ከቀድሞ ሠራዊት አባላት፣ ከዳኞች፣ ከአካል ጉዳተኞች፣ ከመንግሥት ሥራ አስፈፃሚ አካላት፣ ከመምህራን ማኅበር፣ ከንግድ ዘርፍ ማኅበራት፣ ከአሠሪዎች ማኅበራት እንዲሁም ከወጣቶች እና ሌሎች አደረጃጀቶች የመጡ ተባባሪ አካላት ተሳትፈዋል፡፡