ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች ልዑክ ሞሮኮ ገባ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) 40 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች ልዑክ በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ላይ ለመሳተፍ ሞሮኮ ገብቷል።
ልዑኩ በማራካሽ ቆይታው በምርምር የበለጸጉ የጤ እና የኢንቨስትመንት አዋጭ መተግበሪያዎችን ጨምሮ 5 የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ለተወጣጡ ተመራማሪዎችና የቢዝነስ ሰዎች ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።
በኤክስፖው አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ሊያገናኙ የሚችሉ አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶች ይፋ እንደሚደረጉ የልዑካን ቡድኑ አስተባባሪና የአብርሆት ቤተ መጽሃፍት ዋና ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) ተናግረዋል።
የቴክኖሎጂ ተመራማሪዎቹ ለ2 ዓመታት በአብርሆት ቤተመጽሃፍት ሲሰለጥኑ እንደነበር ነው የተጠቆመው፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም በአብርሆት ቤተ መጽሃፍት እና በኤ2 ኤስ ቪ አስተባባሪነት እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡