አቶ መላኩ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር ለአምራች ዘርፉ እድገት ወሳኝ መሆኑን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ በጋራ መስራት ለአምራች ዘርፍ እድገት ወሳኝ ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
በአምራች ኢንዱስትሪዎች በሚስተዋሉ ቸግሮች ዙሪያ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
አቶ መላኩ አለበል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ችግሮች የሚፈቱት የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ በጋራ መስራት ሲችሉ ነው።
ውይይቱ በግሉ ዘርፍና በመንግስት መካከል መተማመንን ለመፍጠር ፣ ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እንደሚያስችል ገልፀዋል።
ከዚህ ባለፈም ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ያስችላል ነው ያሉት።
በዘርፉ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለመቅረፍ መንግስት እየሰራ መሆኑን ገልፀው÷ለውጤታማነቱም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በኤፍሬም ምትኩና ቤተልሄም መኳንት