Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ የ’ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2024′ ኤግዚቢሽንን በይፋ ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የ’ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2024′ ኤግዚቢሽንን በይፋ ከፍተው አስጀምረዋል።

የሀገር ውስጥ ግንባታ እና መሠረተ ልማትን በፈጠራና መፍትሄዎች ለማመላከት ያለመው ”ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2024” ኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ሲ.ደብሊው.ሲ) ድጋፍ እና ትብብር ነው የተዘጋጀው።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተከፈተው ኤግዚብሽኑ÷ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እና የዘርፉ ምሁራን ተገኝተዋል።

ኤግዚቢሽኑ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ከግንባታ አገልግሎት እስከ ስማርት ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎች ያካተተ ነው ተብሏል።

ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2024 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተዋናዮችን አንድ በማድረግ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እድገትን፣ ተግዳሮቶችንና እድሎችን እንዲገነዘቡ ለማድረግ ያመለ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

ኤግዚቢሽኑ ለግንባታ ኢንዱስትሪ ነፃ የመሳተፍ ዕድልን፣ የንግድ አማራጮችን ለማግኘት እና በኢንዱስትሪ ተዋናዮች መካከል ያለውን የግኑኙነት መረብ ለማመቻችት እንደሚረዳም ተመላክቷል፡፡

በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2024 ኤግዚቢሺን ኢትዮጵያን ጨምሮ 24 ሀገራት እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው፡፡

156 ኤግዚቢሽን አቅራቢ ዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ድርጅቶች ሲሳተፉ ፥ ከአነዚህ ውስጥም 115ዓለም አቀፍ ሲሆኑ 41 ደግሞ ሀገር በቀል ናቸው።

22 ተከታታይ ሙያዊ የጎንዮሽ የፓናል ውይይቶች እንደሚኖሩ የተጠቀሰ ሲሆን÷ በዚህም ምህንድስና፣ ፕሮጀክት አስተዳደር፣ ቴክኖሎጂ፣ መሠረተ ልማትና ሕንፃ ግንባታ ዘርፎች ይዳሰሳሉ ተብሏል፡፡

ከግንቦት 22 እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በሚቆየው ኤግዚቢሽኑ÷በአሁኑ ወቅት 4 ሺህ 600 በላይ ጎብኚዎች ቅድሚያ ምዝገባ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ኢንዱስትሪውን አበረታች አቅም ለመገንዘብ ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2024 በርካታ የዲዛይንና ግንባታ እንዲሁም የግንባታ ጥገና እና ፋሲሊቲ አስተዳደር ባለሙያዎችን ጨምሮ ተደማጭነት ያላቸው የኢንዱስትሪ ውሳኔ ሰጪዎች፣ ኤክስፐርቶችና ሃሳቦችን ለመሰብሰብ ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.