የሀገር ውስጥ ዜና

በ24 ሰዓታት ውስጥ 179 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Tibebu Kebede

June 14, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ4 ሺህ 845 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ በ179 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 345 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አስታውቅዋል።